Building Construction / Contract Administration and Supervision

ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ እና አወበል ወረዳዎች የእንስሳት ጤና ኬላዎች ለመስራት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በቁጥር፡ 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመትግበር ከመንግስት የእንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል፡፡

ድርጅታችን በዚህ ዓመት በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ እና አወበል ወረዳዎች የእንስሳት ጤና ኬላዎች ለመስራት እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ይህንንም ለማድረግ ድርጅታችን ብሩክ ኢትዮጵያ ብቁ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ ደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ የጠቅላላ/ህንጻ ስራ ተቋራጭ (GC/BC six and above) ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ሥራዎች የጨረታ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ ቁጥር

የፕሮጀክቱ ስም

 

ወረዳ/ቀበሌ

ስራ ተቋራጭ

የስራው አይነት

 

B-ETH-16/2020

 

Bechena Animal Health Post

 

Enmay / Bechena Town

 

GC/BC-six and ABOVE

 

The main block, dry latrine, soak away pit, guardhouse, shelter, cattle crash & trough and fence, etc

B-ETH-17/2020

 

Lumame Animal Health Post

Awebel / Lumame Town

 

GC/BC-six and ABOVE

 

Main block, dry latrine, soak away pit, guard house, shelter, cattle crash & rough and fence etc

  1. ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ (2012 ..) የታደሰ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት)  ተመዝጋቢ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 1727 ከሚገኘው የድርጅታችን /ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2% ቦንድ በሲፒኦ መልክ  ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲፒኦው የጨረታ ኤንቨሎኘ ውስጥ ለብቻ ታሽጎ መቅረብ  አለበት::
  4. ተጫራቾች በሰም የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ ከላይ በተቁ.2 በተጠቀሰው አድራሻ  በሚገኘው የብሩክ /ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 7:30 ሰዓት ማስገባት  ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማቅረቢያው ሃያኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት  ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  5. ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት፣ ጨረታው በተዘጋበት  ቀን (በተቁ 4 የተመለከተው) ከቀኑ 800 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ስራ ተቋራጩ/ተወካይ  በፈቃዳቸው መገኘት ባይችሉ ወይም በተለያዩ አስገዳጅ ምክያንቶች አሰሪው ድርጅት  ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም::
  7.  ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ከተገኘ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ከባንክ unconditional bank  guarantee ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  8. ተጫራቹ እየሠራቸው ያሉ ተመሣሣይ ስራዎች ካሉት 75% በላይ የስራ አፈፃፀም ላይ የደረሰ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  9. ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ  በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ቀደም ብሎ በድርጅቱ ሥራዎች ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው መብቱ የተጠበቀ ነው::
  10. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 011-661-0069/011-662-1885 በመደወል ወይም በኢሜይል info@thebrookeethiopia.org  አድሻችን መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻችን፣ 22 ማዞሪያ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ ከድልድዩ አጠገብ ነው::

ስልክ ቁጥር፡– 011-6610069/011662-1885

ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ