የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ በቁጥር 7 ያገለገሉ የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተሽከርካሪዎቹ ከሚገኙስት ልደታ ከሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ በራሳቸው ትራንስፖርት የሚያነሱበትን ዋጋ መሆን ይገባዋል፡፡
- ተጫራቶች ለጨረታ የሚወዳደሩበትን ዋጋ /ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመግለፅ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር በመግዛት ቅፁ በሚፈቅደው መሠረት ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታየሚያቀርቡትን ዋጋአዲስ አበባሰሚትበሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ቦታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ባሉት ተከታታይ 7 የሥራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ8ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሚት በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን መኪኖች ከነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ልደታ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ ማየት ይቻላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0966 9312 46 /0911-74 02 25 በመደወል መጠየቅ ይችላል፡፡
ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ