የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በሴክተር መ/ቤቶች
- የቢሮ የጽ/መሣሪያ
- የጽዳት ዕቃዎችን
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
- ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎችን
- የፈርኒቸር ውጤቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- ተጫራቾች በ2012 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ለሚያቀርቡና ታክስ ክሊራንስ አቅራቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 5000 ሺህ ሲፒ ኦ ማስያዝ የሚችል
- ተጫራቾች ህጋዊፈቃዳቸውንና ተእታቫት የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጥቅል የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በወንዶ ገነት ወረዳ ገቢዎች ባቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ ከፍለው የከፈሉበትን ደረሰኝ በማቅረብ ሰነዱን ከወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ኢኮል/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒዎች ለየብቻ በሰም ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00-5፡00 ሰዓት በወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የወቅቱንዋጋያላገናዘበ የጨረታዋጋተቀባይነት አይኖረውም ከቀረቡት የወቅቱን ዋጋ ትንታኔ እንድያቀርቡ ይደረጋል፡፡
- የአሸናፊ ተጫራች ያሸነፋቸውን ዕቃዎች እስከ ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታ አይገደድም፡፡
ማሳሰቢያ፡–ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462220418 (0462220429)
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት