Motorcycles and Bicycles Purchase / Tri Wheeler

ወላይታ ልማት ማህበር ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ወልማ 009/2013

ወላይታ ልማት ማህበር እ.ኤ.አ 2020/ ወይም 2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለልማት ማህበሩ እና በሥሩ ለሚተዳደሩ ፕሮጀክት የሞተር ሳይክል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን፡- 

 • ሎት፡-1 ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶና ግዴታዎች
 1. በግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
 3. ተጫራቶች ሁሉንም ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 100 ብር በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ በተከታታይ እስከ ዐኛው ቀን ድረስ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትሰን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ቢሮ እና በወላይታ ሶዶ ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ከሚገኘው ግዥና ንብረት አስተዳደር ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቶች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማስላት 2% በባንክ የተመሰከረ በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሰራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 5% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ብር በመሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል፡፡
 6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አላቀርብም ማለት የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል፡፡
 7. ተጫራቾች የዋጋማቅረቢያውንና የመወዳደሪያፖስታቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ልማት ማህበር ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. የጨረታ ፖስታ በጨረታ ሣጥን የሚገባው የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድ ላይ ጨምር በተከታታይ እስከ 10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ ገቢ ሆኖ ልከ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ግዥና ን/አስ/ር ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 በይፋ ይከፈታል፡፡ አስረኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሕጋዊ በዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
 9. አንድ ተጫራች የሚያሠራው ሲፒኦ በሕጋዊ ባለመብት ወይም ድርጅት ስም መሆን አለበት፡፡
 10. አሸናፊው ተጫራች በሚገባው ውል መሰረት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪና በማጓጓዣ በማምጣት ለማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በአድራሻው ያስረከባል፡፡
 11. አንድ ተጫራች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ካለው ለተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በየሎቱ የተዘረዘሩ ዕቃዎች በመሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
 12. ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩባቸውን የዕቃ አይነቶች ለይተው መጻፍ አለባቸው፡፡
 13. ማህበሩ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት 20%-30% እንደአስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም መቀነስ መግዛት ይችላል፡፡
 14.  የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆነው ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 • ማሳሰቢያ :ማህበሩ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046/1801191/01111572842  መጠቀም ይችላሉ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር