የጨረታ ማስታወቂያ
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2012 በጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን፡
- LAN Infrastunucrure project Wollega University Grimbl Campus
- Network Adge Redendency at Wollega University main Campus
- Collaborative Sman Class Room
- Unified WLAN infrastructure
- Virtual Desktop Infrastructure system Wollega University Nekemte Campus ፕሮጀክት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት የዓመቱን ግብር የከፈሉ፣ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የግዥ ቡድን አስተባባሪ ቢሮ ቁጥር 109 አዲሱ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በሙሉም ሆነ በከፈል ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሠነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 109 አስተባባሪ ቢሮ አዲስ ሕንፃ ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የግዥ ቡድን አስተባባሪ ቢሮ ቁጥር 109 አዲሱ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሠነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሠነዶች የሚከተሉት ናቸው ::
- ሀ. የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
- ለ. ከፌዴራል ሀገር ወስጥ ገቢ ወይም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን የተወጡና በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ የአቅርቦት የምስክር ወረቀትና የሚጫረቱበትን ዋጋ ከብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሐ. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሠነድ ጋር የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡
- መ. ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) መጠን በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸ ሲሆን፣ አቀራረቡም በሲፒኦ የሚያዘው ጥሬ ገንዘብ ሆኖ ይህም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ብቻ ሆኖ ሲፒኦውን ከጨረታ ሠነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሠ. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡ – አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ መድኃኒአለም ት/ቤት አለፍ ብሎ በፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ ቤት እና በገነት ቤ/ክርስቲያን መካከል በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ፅግሸት ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ፡፡
ስልከ ቁጥር፡– 0113492685/01188294 47
አዲስ አበባ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 0578999911/12
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ