Catering and Cafeteria Services / Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Computer and Accessories / Equipment and Accessories / Furniture / Garments and Uniforms / Hand Tools and Workshop Equipment / House Furniture / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Office Machines and Computers / Printed Advertising Materials / Printing and Publishing / Stationery / Textile

ኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ዋና የስራ ሂደት በ2013 የበጀት ዓመት ባለው በጀት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ

ወረዳ 05 ፋይናንስ /ቤት

የተጫራቾች መመሪያ

ኮ/ቀ/ክ/ከተማ  የወረዳ 5 ፋይናንስ /ቤት የመንግስት ግዥ ዋና የስራ ሂደት 2013 የበጀት ዓመት ባለው በጀት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።

 • ሎት አንድ የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ /ስቴሽነሪ/
 • ሎት ሁለት የተለያዩ የደንብ ልብስ
 • ሎት ሶስት የተለያዩ የጽዳት እቃዎች
 • ሎት አራት ቋሚ ዕቃ
 • ሎት አምስት የፈሪንቸር ጥገና
 • ሎት ስድስት የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
 • ሎት ሰባት ህትመት አገልግሎት
 • ሎት ስምንት መስተንግዶ አገልግሎት
 • ሎት ዘጠኝ ጉልበት አገልግሎት ለመግዛት ስለፈለግን ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች በሚገባ በመረዳት በጨረታ ሰነድ ላይ እንዲሞላ ያስፈልጋል።
 1. የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን መግባት ይኖርባታል።
 2. ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 9 ባሉት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ
 3. ተጫራቹ በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት ላይ የጨረታ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ 5000 /አምስት ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ በመስሪያ ቤታችን ስም በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖባቸዋል።
 4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች የእያንዳንዱን ዋጋቫትን ጨምሮ በግልፅ ማስፈር ይኖርበታል።
 5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት በይፋ ኣየር ላይ ከቆየ በኋላ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓምተዘግቶ በማግስቱ ጥቅምት 19 ቀን 2013 . 430 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
 6. እያንዳንዱ ተጫራች ስለሚያቀርባቸው ዕቃዎች አጭር መግለጫ የዕቃው አምራች የተሰራበት ሀገር ሞዴል ስማቸው አድራሻቸውና ፈርማቸው እያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም በማህተም አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው።
 7. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይንም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃው አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 8.  በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ዕቃዎቹን ከጽ/ቤቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት እንዲያስገባ ሲታዘዝ በወረዳ 05 ዕቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ በራሱ ወጪ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
 9. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
 10. በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ውል እንዲፈጽምና ውል ማስከበሪያውን እንዳስያዘ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ተመላሽ ይደረግለታል።
 11. ማንኛውም ተጫራች የመ/ቤቱ የዕቃ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የዕቃዎችን ጥራት አይቶ /ቤቱ ካወጣው የጨረታ ሰነድ እና በጨረታ እንዲያልፍ ከተደረገው የዕቃው ቴከኒካል ስፔስፊኬሽን ወይም ከገባው ናሙና ጋር የማይጣጣም ከሆነና ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ጨረታውን  አሸንፎ እንዲያቀርብ የታዘዘው ድርጅት ዕቃውን የመመለስ ግዴታ አለበት።
 12. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች ማሸነፉን እንደተገለጸለት ከመ/ቤቱ ጋር 7ኛው – 10ኛው ቀን ባሉት 4 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት።
 13. በጨረታው የሸነፈባቸው ዕቃዎች ውል ከፈጸመ በኋላ በሚቀጥሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃዎችን በወረዳ 05 ዕቃ ግምጃ ቤት ገቢ ማድረግ አለበት።
 14. የግዥ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ ሰነዱ ላይ የተሰጠው የዕቃ ብዛት በተወሰነ መጠን 20% ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት።
 15. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብሎ ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎችና ናሙና ለዕቃ ግምጃ ቤታችን ማስረከብ አለባቸው።
 16. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የጨረታ ኮሚቴው የዕቃዎችን ጥራት በድርጅቱ የስራ ቦታ በመገኘት ለማየት ቢፈልግ ድርጅቱ ተገቢውን ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት
 17. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ድርጅቶች ማሸነፋቸው እንደተገለጸለት በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈጸመ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ /ቤቱ እንደምርጫው ሁለተኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል።
 18. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ

 • ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው
 • ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃዎች ልዩ መለያ ማቅረብ ከፈለጉ ምርመራ በሚለው ቦታ መፃፍ ይችላሉ
 • አስፈላጊ ሲሆን የጨረታ ኮሚቴው ወይም የግዢ ሰራተኛው በቂ ስቶክ መኖሩን ለማረጋገጥ መጋዘን ማየት ይችላሉ፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0911046187/0913906133 ወይም 01113-69-66-04

///ከተማ የወረዳ 5ፋይናንስ

/ቤት የመንግስት ግዥ ዋና

የስራ ሂደት