House and Building Foreclosure / House and Building Sale

ኮንዶሚንየም ቤት የሐራጅ ሽያጭ

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ እልፍነሽ ማሞ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አስማማው ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 153044 30/9/2011 ዓ.ም እና መ/ቁጥር 92953 22/6/201 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 ህ/ቁጥር 42 የቤት ቁጥር 39 የሆነ ኮንዶሚንየም ቤት ቤቱ በአቶ አስማማው ታደሰ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የቤቱ ስፋት 46-29 ካ.ሜ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወሰዱት ብድር ያልተከፈለ ቀሪ ብድር ዕዳ እስከ ሰኔ 2011 ዓ.ም ድረስ ብር 12,727.72 ዕዳ ያለበት መሆኑ ታውቆ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋብር 191,473.96 ሳ (አንድ መቶ ዘጠና አንድ ሺ አራት መቶ ሰባ ሶስት ብር ከዘጠና ስድስት ሳንቲም ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቶች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቶች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቶች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቶች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት