ማስታወቂያ
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘውን ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አገልግሎት የሚውል
- የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣
- የህንፃ መሳሪያዎችን፣
- የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ
- የተለያዩ የአውቶሞቲቭ እቃዎች፣ እንዲሁም
- የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም :-
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥርና የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የግዥው መጠን ከ50,000 ብር በታች ከሆነ ድርጅቱ በስማቸው የታተመ የ2% ደረሰኝ ሊኖራቸው ይገባል።
- ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በአንድ ሎት በመክፈል ከኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 007 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጠቅላላ ዋጋ ድምር 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPOወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የሚወዳደረው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሽነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 007 መጥተው ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከብር 20,000 በላይ ለሚፈፀመው ግዥዎች መ/ቤቱ 7.5 ቫት የሚሰበስብና ለዚህም ህጋዊ ደረሰኝ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን አሸናፊ ድርጅት እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት የኮሌጁ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡033 551 24 90
ደውለው ይጠይቁ
በአብክመ ቴክኒክና ሙያ ኢ/ል/ቢሮ
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን