ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር በኮምቦልቻ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች የ2013 በጀት አመት
- ጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- ቋሚ እቃዎች፣
- የግንባታ እቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጐማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተወዳዳሪዎች ዕቃዎቹን ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ያደሰ መሆን አለበት።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት የተመዘገበና የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00/አምስት ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቢሮ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል።
- ተወዳዳሪዎች ማንኛውም ከሙስና ወንጀል እና ኪራይ ሰብሳቢነት ነጻ መሆን አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ ለአሸናፊው እቃዎች በተባለበት ቦታ ማድረስ የሚችልና ያሸነፈበትን እቃዎች በተባለበት አቅም ያለው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር150.00 በመክፈል በምስ/ሐ/መስ/የኮምቦልቻ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ቢሮ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- እቃዎች በኢትዮጵያ ማቴሪያል እስታንደርድ የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው። በዚህ ያልተረጋገጠ እቃ ካላቀረቡ መ/ቤቱ እንደማይቀበል ማወቅ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0915041538/0915042915
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር በኮምቦልቻ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት