ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮ/ቻ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት የኮ/ቻ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ካፒታል በጀት በ2013 በጀት አመት በተያዘው በጀት
- Design and supervision work for Albiko Bridge በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO. /ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር /እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሙያ ከደረጃ ከ3/ሶስት/ በላይ ሆኖ የታደሰ ሙያ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-5 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮ/ቻ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 በመሄድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት 11:30 ድረስ ከ12/2/2013 እስከ 2/3/2013 ዓም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በcpo ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ 4000/አራት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- Design for Albiko Bridge ስራዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- supervision Work for Albiko Bridge ስራዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮቻ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰእት 3/3/2013 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል ነገር ግን የተለየ ችግር ካጋጠመ ከቅዳሜና እሁድ ውጪ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲገጥማችሁ አሰሪው መ/ቤት ጨረታ ካወጣው አካል ከጨረታው መከፈቻ እለት በፊት በስልክ ቁጥር 0338514142/0338514113 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮምቦልቻ ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት