ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃያተየግማ
Commercial Nomminees PLC
CN/NCB/02/2013
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከዚህ በታች በሎት የተገለጹትን አገልግሎቶች የተለያዩ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
- ሎት 1፡– ገርጂ መብራት ኃይል አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱን ህንፃ እድሳት።
- ሎት 2፡– ሳርቤት ገብርኤል አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱን ህንጻ እድሳት።
- ሎት 3፡– በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ተገንብቶ የሚገኘውን ስቲል ስትራክቸር አፍርሶ ወደ ድርጅታችን መጋዘን ማስገባት።
- ሎት 4፡– የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ግዢ።
በመሆኑም ለሎት 1፣ 2 እና 3 ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ የገቢዎች ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለሎት 1፣2 እና 3 የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የመሳሰሉት በሰም በታሸገ የተለየ ኤንቨሎፕ እንዲሁም የመጫረቻ ዋጋ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለኃይማኖት ቅርንጫፍ በሚገኝበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 18 ሎጀስቲክስ እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዋና ክፍል ብር 100 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡30-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00/ ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪ ቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ።
ስልክ ቁጥር 0111475611
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር