CN/NCB/01/2013
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከዚህ በታች በሉት የተገለጹትን አገልግሎቶች የተለያዩ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1፡– ለቢሮ የሚሆን የህንጻ ኪራይ አገልግሎት ግዢ፡
- ሎት 2፡– በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተገንብቶ የሚገኘውን ስቲል ስትራክቸር ነቅሎ ማንሳትና ወደ ድርጅታችን መጋዘን ማስገባት፡፡
- ሎት 3፡– ገርጂ የሚገኘውን የድርጅቱን ህንጻ እድሳትና አጥር ስራ፡፡
- ሎት 4፡– ሳር ቤት ገብርኤል የሚገኘውን የድርጅቱን ህንጻ እድሳት ስራ።
- ሎት 5፡– ቃሊቲ የሚገኘው የዛክ መጋዘን የፈረሰ አጥር እድሳት ስራ፡፡
- ሎት 6፡– ደረጃውን የጠበቀ የአፍ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) በማእቀፍ ግዢ የሚፈጸም፡፡
በመሆኑም ከሎት 2 እስከ ሎት 5 ላሉት ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ስራ ተቋራጫች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የመሳሰሉት በሰም በታሸገ የተለየ ኤንቨሎፕ እንዲሁም የመጫረቻ ዋጋ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለኃይማኖት ቅርንጫፍ በሚገኝበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 118 ሎጅስቲክስ እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00 -6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00 -11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000.00 ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሀምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለሀይማኖት ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንጻ
ስልክ ቁጥር 011-1475611