የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 04/2012
ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአቶች ኢንዱስትሪልማት ኢንስቲትዩት ለ2012 የበጀት ዓመት የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1 የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/12
- ሎት 1, ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎች
በዚህም መሠረት በጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ መወዳደር እንዲችሉ፣
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
- የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑና በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን ፈቃድ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣
- ለመንግሥት መ/ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ (WWW.ppa.gov.et) ላይ የተመዘገቡ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣
- የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN) ምገባ የምስክር ወረቀት እና
- ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አባሪ የተደረገውን የፀረ–ሙስና ቅጽ በድርጅቱ ኃላፊ ተሞልቶ ተፈርሞና ማህተም ተደርጎበት ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የተዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመከፈል ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው ጎዳና በአንበሳ ጋራዥ ታጥፎ ወደ መብራት ኃይል ኦልማርት ሱፐር ማርኬት አጠገብ ከሚገኘው መ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 1 መወሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስላቸው የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ለሎት 1 ብር 200,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ( ሲፒኦ) መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓም ከጠዋቱ፡ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 6 39 41 27 /0911 13 45 45 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኬሚካል ኮንስትራክሽን ግብዓቶች
ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት