የጨረታ ማስታወቂያ
ካፋ የጫካ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ለቡና ምርት ዝግጅት አገልግሎት የሚውሉ
- (ሀ) ርዝመት 30 ሜትር ስፋት 2 ሜትር የሆነ ደረጃውን የጠበቀ ጋልባናይዝድ የቡና ማድረቂያ ሽቦ ብዛት በጥቅል 800
- (ለ) ርዝመት 30 ሜትር ስፋት 2 ሜትር የሆነ በቡና ማድረቂያ አልጋ ላይ የሚዘረጋ መረብ /ኔት/ ደረጃውን የጠበቀ ብዛት በጥቅል 500
- (ሐ) የቡና መሸፈኛ ፕላስቲክ/ ሸራ ደረጃውን የጠበቀ ብዛት በጥቅል 300 በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዕቃ ነጠላ ዋጋ ለይተው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ከዩኒየኑ ዋና መ/ቤት ቦንጋ ወይም ከኤከስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት /አዲስ አበባ/ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒየኑ ዋና መቤት (ቦንጋ) ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በዩኒየኑ ዋና መ/ቤት (ቦንጋ) ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ተሟልተው ባይቀርቡ በተገኙት ብቻ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላም ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 047 331 0790/011470 3396 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ካፋ የጫካ ቡና ገበሬዎች
ኅብረት ሥራ ዩኒየን