የጨረታ ማስታወቂያ
ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1/ የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 2/ የደንብ ልብስና ቆዳ ጫማዎች
- ሎት 3/ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 4/ ተንጠልጣይ ሌዘር ቦርሳዎች
- ሎት 5/ የስፖርት ትጥቅና ዕቃዎች
- ሎት 6 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- ሎት7 / የህንጻ መሣሪያዎችና የቧንቧ ዕቃዎች
- ሎት 8/ የመጋረጃ ጨርቆችና ብረቶች
- ሎት 9 /የህክምና ዕቃዎችና ኬሜካሎች
- ሎት 9/ የተለያዩ መጻሀፎች
- ሎት 10 / ህትመቶች
- ሎት 11/ ሰነድ መያዢያ ካልኩሌተር ያለው ቦርሳ
- ሎት 12 / ፎቶ ኮፒ ፡ ማባዣ ፤ፕሪንተር ፤ ኮምፒውተር ፡ ላፕቶፕ ጥገናዎች
ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱት ዕቃዎች ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- የዘመኑ ግብር የከፈለ
- የቫት ከፋይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያና የቲን ቁጥር የሚቀርብ
- የጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ ማስረጃ የሚያቀርብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ተጫራቾች የግዥ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ማሳያዥያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር /በመክፈል ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስተዳደር መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ / ቢንድ ቦንድ ወይም 3000.00 / ሶስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው እስከ አስረኛው የስራ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 2.30 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው 11 ቀን ልከ ከቀኑ በ5.00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም እንዲሁም ከተጠየቀው ከእስፔስፊኬሽን ውጪ ዕቃ ማቅረብ አይፈቀደም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው ::
- በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸውን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ግቢ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- አድራሻ፡– ፈረንሳይ ለጋሲዮን ልዩ ስሙ ጉራራ 2 ቁጥር እና 55 ቁጥር አውቶብስ ማዞሪያ ከኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በስተጀርባ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማስረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 -114-02-96/011-114-49-86/0913043821/0111549331 በመጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ
በየካ ክ/ከ ትምህርት መምሪያ የከፍተኛ
12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት