የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኤ/አ/ማ/001/13
የሾሪንግ /Shoring/ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር አዲስ አበባ 22 አካባቢ ሌክስ ፕላዛ በስተጀርባ ለሚያስገነባው ባለ 15 ፎቅ ሕንፃ የሾሪንግ ሥራ በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
በመሆኑም፡
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ሰርተው ላጠናቀቋቸው ፕሮጀክቶች የምስክር ወረቀት /Certificate of Successful completion/ ማቅረብ የሚችሉ::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በድርጅታችን ትክክለኛ ስም ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት/ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 – 11፡30 እና ቅድሜ 2፡30 – 6፡00 ሰዓት ድረስ/ 5 /አምስት/ ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አጠገብ ማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መ/ቤት የሎጀስቲክስ እና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- አክሲዮን ማኅበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር
011 868 84 50/51/ ሞባይል 0930 36 42 61
E-mail: gm@esdros.com
P.O.Box 33128