የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኤ/አ/ማ/002/13
የዲዛይን ክለሳ የግንባታ ጥራት ቁጥጥር እና
ኮንትራት አስተዳደር ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር አዲስ አበባ 22 አካባቢ ሌክስ ፕላዛ በስተጀርባ ለሚያስገነባው ባለ 15 ፎቅ ሕንፃ የዲዛይን ክለሳ የግንባታ ጥራት ቁጥጥር እና ኮንትራት አስተዳደር በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ደረጃ 3 /ሦስት/ እና ከዚያ በላይ አማካሪ ድርጀቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፊሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ሰርተው ላጠናቀቋቸው ፕሮጀክቶች የምስክር ወረቀት /Certificate of Successful completion ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በድርጅታችን ትክክለኛ ስም ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅደመ ሁኔታ ላይ ያልተሰመረተ የባንክ ጋራንት (unconditional bank gurantee) ማያያዝ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 11፡30 እና ቅዳሜ 2፡30 – 6፡00 ሰዓት ድረስ/ 5 /አምስት/ ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አጠገብ ማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መ/ቤት የሎጀስቲክስ እና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ኢክሲዮን ማኅበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።
አድራሻ
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር
01 1 168 84 50/51
ሞባይል 0930 36 42 61
33128
E-mail: gm@endros.com