የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
ኤም ዋይ ኤም ዩዝ ቢዩልዲንግ ኢንሹቲንግ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን ሀገር በቀል ድርጅት በኢብሳስ የሂሳብ ስታንዳርድ /PSAS/ መሰረት የሂሳብ እንቅስቃሴዎች ህጋዊ እውቅና ባላቸው ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- የ 2011 በጀት ዓመት መነሻ በማድረግ (financial position) ሪፖርት ብቻ
- እአአ ከሐምሌ 1/2011 እስከ ሰኔ 2012 ያለውን አንድ ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴ ማስመርመር እንፈልጋለን፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቱ በሚገኝበት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ስሙ ቤተል አካባቢ በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የፋይናንስ ኦዲት ሙያ ምስክር ወረቀት ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማሳሰቢያ:-
- ተጫራቾች አገልግሎት ዋጋ ታክስን ጨምሮ እና የሂሳብ ምርመራ የሚጠናቀቅበት ጊዜ በግልፅ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሌላው ተጫራች ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም። ኤም ዋይ ኤም ዩዝ ቢዩልዲንግ
ኢንሸቲንግ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን