ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
I.ኢፌዴሪ ስኳር ኮርፖሬሽን የኦሞ ኩራዝ ሦስት ስኳር ፋብሪካ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎችን ፣ ባትሪዎችን እና የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ካሪትረጆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
II. የሻጭ አድራሻ (ዕቃው ወይም ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ ክልል፡ ደቡብ ብ/ብ/ህ ዞን ምዕራብ ኦሞ ፤ወረዳ ማጂ ወረዳ ኦሞ ኩራዝ ሦስት ስኳር ፋብሪካ ጊቢ
III. ብዛት በሎት 1፣ 100 ቶን የተለያዩ ዓይነት ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና በሎት 2፣ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ባትሪዎች እና የፕሪንተሪና ፎቶ ኮፕ ካርቲሬጆች
IV. ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ጨረታውን ለመግዛት ማመልከቻ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት በማቅረብ እና የማይመለስ ብር 100 በመቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚከተለው አድራሻ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ኦሞ ኩራዝ ሦስት ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ
ቢሮ፤ አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ከፈዴራል ፖሊስ ዋና
መ/ቤት ወደ ልደታ ቤተ ክርስቲያን በሚወስደው ዋና
መንገድ ፊሊፕስ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 406 ነው፤
ስልክ ቁጥር 0913266284 ወይም 0909197853
በኢ–ሜል omo3service2020@gmail.com
ፖ.ሳ.ቁ አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ፤
V ተጫራቾች ከሚያቀርበት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተቁ viii. የተገለጸውን የገንዘብ መጠን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
VI. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (ኣንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7:30-11፡00 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30 -6፡00) ከላይ በተራ ቁጥር-4 በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
VII. መወዳደሪያ ሰነድ የሚቀርብበት፣ የጨረታ ሳጥን የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን፤ወር፤ ዓ.ም እና ሰዓት፡– ጨረታው ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ የጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር iv በተገለፀው አድራሻ ጨረታው ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
VIII. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ፡
- በሎት 1 ለተጠቀሱ ለተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ እና
- በሎት 2 ለተጠቀሱ ላገለገሉ ጎማዎች፣ ባትሪዎች እና ለፕሪንተርና ቶነር ቀለሞች 5,000 (አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ የዋስትና ደብዳቤ ካደራጀው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
IX. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት 7(ሰባት) ቀን በኋላ ባሉ 10(አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ/CPO/ በማቅረብ ውል መግባት አለበት::
X. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሽነፈውን ዕቃ ክፍያ መሉ በሙሉ ማጠናቀቅ አለበት፣
XI. ጨረታ አሸናፊው ክፍያውን ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አንድ ወር ወይም 30(ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት፡፡
XII. ረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት ነው፡፡
Xlll. ፋብሪካ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሞ ኩራዝ 3 ስኳር ፋብሪካ