የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኢንህንሲንግ ፓስቶራሊስት ሪሰርች ኤንድ ዴቨሎፕመንት ኦልተርኔቲቭስ (ኢፓርዳ) ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እና እንዲሁም በኢትዮጵያ እና ኪኒያ ከሚገኙ ሌሎቸ አምስት አጋር ግብረሰናይ ድርጅት (VSF Germany, Vita/RT, Mercy Cops, TUPAD and CIFA ጋር በትብብርና VSF Germany የሚመራ Omo Delta Project – Expanding the Rangeland to Achieve Growth and Transformation የተሰኘ ፕሮጀክት እየተገበር ይገኛል። ኢፓርዳ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ ልዩ ልዩ የንፅህና መጠበቂያ እና የጽዳት ዕቃዎችን ማቅረብ ይገኝበታል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማቅረብ የምትችሉ እና መስፈርቶች የምታሟሉ አምራቾች፣ አቅራቢዎችና አከፋፋዮች በጨረታው እንድትካፈሉ ይጋብዛል።
ለግዢ የሚፈለጉ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ |
|||
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
ብዛት |
ዝርዝር መግለጫ |
1 |
ሳኒታይዘር (Sanitizer) |
1000 ሊትር |
|
2 |
ፈሳሽ የእጅ ሳሙና |
3400 ሊትር |
|
3 |
ፈሳሽ ሳሙና |
6000 ሊትር |
|
4 |
ፈሳሽ በረኪና (bleach) |
600 ሊትር |
|
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በ2012 የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ወረቀት
- የምግብ ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው
- የኢትዮጵያ ደረጃዎች መዳቢ ኤጀንሲ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው
- እያንዳዱ ምርት የተመረተበትን ቀን እና አገልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን በግልጽ የተቀመጠ እና በምርቱ ላይ መያዣ ላይ የታተመ መሆን አለበት
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ከአንዳንድ ናሙ እና እንዲሁም ከ2% ጨረታን ማስከበሪያ ሲፒዩ (CPO) ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው ዋስትና በድርጅታችን ስም “Enhancing Pastoralist Research & Development Alternatives (EPRDA)” በሚል የሚቀርብ መሆን አለበት።
- ጨረታው ታህሳስ 17 ቀን 2013 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻ መድረስ አለበት። የተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ እና ተያያዥ ሰነዶችን በሰም በታቸገ ፖስታ የሚቀርብ መሆን አለበት።
- ጨረታው ታህሳስ 17 ቀን 2013 ከቀኑ 5:00 በኢፓርዳ ዋና መስሪያቤት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- በተጨማሪ አሸናፊው አቅራቢ ዕቃዎቹን ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ማቅረብ አለበት::
- ኢፓርዳ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
- አድራሻ የረር በር- ከጃክሮስ አደባባይ – ወደ ጎሮ የሚወስደው መንገድ ከሌቃ ህንጻ ጀርባ ስልክ፡ +251978118982