ethio telecom
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግንባታ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት በሪጅኑ ስር ለሚሰሩ የጄኔሬተር (ታንከር እና ትራንስፎርመር ፋውንዴሽን የግንባታ ስራ በአ/ምንጭ ፤ተርጫ አረካ ሃላባ ዱራሜ ፤ ሺሺቾ፣ ሳውላ ባስኬቶ፤ ሆሳዕና ፤ ቡታጅራ፤ ወልቂጤ ፁና ወላይታ ሶዶ በጨረታ ቁጥር 4040191 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ኣገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል ፡፡ ስራዎቹ በ ስድስት (6 ) ፓኬጅ የተከፈሉ ሲሆኑ በደረጃ ሰባት እና ከዚያ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች ፤ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከወላይታ ሶዶ ሪጅኑ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 በአካል በመቅረብ የማይመለስ 100 ብር ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወላይታ ሪጅኑ ፅ/ቤት በ 25/02/2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ በ 26/02/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል፡፡
ፓኬጅ |
ቦታው |
ስራው |
አንድ |
አርባ ምንጭ |
ጀነሬተር፣ታንከር እና ትራንስፎርመር ስራ |
ሁለት |
ቡታጅራ እና ወልቂጤ |
ጀነሬተር ውል ታንከር እና ትራንስፎርመር ቤዝ ፋውንዴሽን ስራ |
ሶስት |
ሆሳዕና |
ጀነሬተር ፊውል ታንከር እና ትራንስፎርመር ቤዝ ፋውንዴሽን ስራ |
አራት |
ሳውላ እና ባስኬቶ |
ጀነሬተር እና ታንከር ፋውንዴሽን ስራ |
አምስት |
ወላይታ አረካ እና ተርጫ |
ፈውል ታንከር ፤ ባትሪ ካብኔት ትራንስፎርመር ቤዝ ፋውንዴሽን ስራ |
ስድስት |
ሀላባ ፣ዱራሜ እና ሾኔ |
ጀነሬተር ታንከር እና ትራንስፎርመር ቤዝ ፋውንዴሽን ስራ |
መስፈርቶች
- የጨረታ ማስከበሪያ አስራ አምስት ሺህ (15,000.00) ማቅረብ የሚችል
- በደረጃ ሰባት ቢያንስ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚች ል፣ የክፍያ ሰርተፍኬት እና የስራ ውል ኮፒ አብሮ ማያያዝ ይኖርበታል ፤
- የ2012 ዒ.ም ግብር የከፈለ እና ታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
- ከዚህ በፊት በድርጅታችን ስሪ ወስዶ በገባው ውል መሰረት ስራውን ያላጠናቀቀ ድርጅት በዚህ ጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶከመንት ዋናው እና ኮፒውን እንዲሁም ሲፒኦ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አንድ ድርጅት ከአንድ ፓኬጅ በላይ መሳተፍ ይችላል ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የኢትዮ ቴሌኮም ዋናው መ/ቤት