ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በጃራ ኪዎስክ ሾፕ የሪኖቬሽን ስራ REQ4046343 በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 19/ 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመ/ቤቱ ሶርሲንግ ከፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
መስፈርት
- ጨረታው ከታህሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 19/2013 ከቀኑ 5:30 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተ. እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሰሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 5000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲፒኦ በኢትዮ ቴሌኮም ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ፅፈው መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ቀኑ 5:30 ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ይከፈታል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲፒኦ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0221-110994/0221-121660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም
ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን