የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ለተለያዩ የመ/ቤቱ የሚውሉ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመስከረም 25 ቀን 2013 እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓም ከሰኛ እስከ ዓርብ በስራ ሰዓት አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 አንድ መቶ ብር በመክፈል የጨረታውን ሠንድ በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) 50,000 (ሀምሳ ሺ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ የጨረታውን ስም፤ የተጫራቹን ሙሉ ስም እና አድራሻ በትክክል መጻፍ አለባቸው፡፡
- የድርጅቱን የባንክ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ባንክ ስቴትመት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ ስታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 022-111-0994/022-112-3550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን