የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን አዳማ በሪጅኑ ቢሮ የንጣፍ ሥራ REQ No: 4046644 ግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሦስት ዓመት የሥራ ልምድያላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሣስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ አዋሽባንክ ሕንፃ ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
መስፈርት:-
- ጨረታው ከህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣የተፈታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉመሆን ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረትማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲፒኦ በኢትዮቴሌኮም ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸዉ ላይ ስማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸዉን በትክክል ጽፈዉ መፈረም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ ስታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባትይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም
ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን