የስታርተር ባትሪ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ሪጂን ጽ/ቤት ስታርተር ባትሪ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላችሁና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሐዋሳ ዋናው ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 307 በመቅረብ የማይመለስ 100 ብር ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ |
የሳይት ቦታ |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መከፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር
|
1 |
ሐዋሳ ጽ/ቤት |
4046201 |
ለ15 ቀን |
ህዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት |
ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት |
10,000.00
|
መስፈርት –
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል።
- የ2012 ዓም ግብር የከፈለ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የቫት እና የቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- በገቢዎች አስተዳደር ባለስልጣን በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ያለው እና ደብዳቤውን ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ፋይናንሻል ዋናው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ዶክመንት ዋናው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ሁለት ኮፒ ) ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒውን (ሁለት ኮፒ) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም ሲፒኦ ለየብቻ አድርገው በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም