Vehicle (garage service)

ኢትዮ- ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና /ሰርቪስ ስራ ላይ የተሰማሩና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

በኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተሽከርካሪዎች የጥገና /ሰርቪስ/ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

ኢትዮ- ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃየተየግ.ማ. የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና /ሰርቪስ ስራ ይ የተሰማሩና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። 

ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በኢትዮ- ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ኮርፖሬት ግዥ መምሪያ ቀርበው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በጨረታው መወዳደር ይችላሉ። 

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ማንኛውም ተጫራች እስከ ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓም ከ ቀኑ 08.00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዶችን ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም። በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች በቀረቡት ዝርዝር መስፈርቶች መሰረት መወዳደር ይችላል። 

የተጫራቾች መመሪያ 

 •  በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ቫት (VAT) እና ቲን (TIN) ሰርተፍኬት ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። 
 • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና “ኢትዮ-ሌዘርኢንዱስትሪ ኃየተየግ.ማ (Ethio-Leather lndustry PLC)“ ስም ማስያዝ አለባቸው።
 • ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ ቀናት ሳሪስ በሚገኘው የኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኮርፖሬት ግዥ መምሪያ የማይመለስ ብር 200.00 |ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ህጋዊ ወኪል በሚልኩበት ወቅት በሰነዶች ማረጋገጫ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 
 • ተጫራቾች በሚያስገቡት ዋጋ ለአንድ አመት የአገልግሎት ሽያጭ ውል የሚፈርሙ ይሆናል። 
 • ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በካሽ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማቅረብ በአምስት ቀናት ውስጥ ውል መፈጸም ይኖርበታል። 
 • የአከፋፈል ሁኔታው 100% ከአገልግሎት አቅርቦት በኋላ ይሆናል።
 • ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ሰነድ ውስጥ የተዘረዘሩት አገልግሎቶች ሁሉ ላይ ዋጋ ማቅረብ የኖርባቸዋል፡፡
 • . በዚህ የጨረታ ሰነድ ውስጥ የተካተቱት እና በተጫራቹ ተሞልተው ሊቀርቡ የሚገባቸው ቅፆች በሙሉ በአግባቡ ተሞልተው፣ ተፈርመው እና ሁሉም ገጽ ላይ ማህተም ተደርገው መቅረብ አለባቸው። 
 • ድርጅቱ እንደአስፈላጊነቱ የተጫራቾችን ወርክሾፕ ወይም የመስሪያ ቦታ እና ፋሲሊቲ በአካል በመገኘት ግምገማ ሊያደርግ ይችላል።
 • . የድርጅቱ የስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ ከ 2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ነው።
 • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ሲያቀርቡ የሚከተሉት መካተት አለባቸው።
 • ከጨረታ ሰነድ ጋር በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣
 • ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር)፣
 • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት 
 • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 • በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ በመመርኮዝ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
 • የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋውና ጨረታው የሚከፈተው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በአስራ አንደኛው ቀን ማለትም — 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሳሪስ ሬስ ኢንጂነሪንግ ፊት ለፊት በሚገኘው ዩኒቨርሳል የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ ኮርፖሬት ግዥ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ይሆናል። የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 
 • የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም በብሄራዊ በአላት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተቀመጠው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

አድራሻችን : ሳሪስ ሬስ ኢንጂነሪንግ ፊት ለፊት በሚገኘው ዩኒቨርሳል የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ ኮርፖሬት ግዥ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ይሆናል ስልክ 

ቁጥር 0911147898 

ኢትዮ-ኤዘር ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማኅበር