የሸቀጥ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ አምራች እና አከፋፋዮችን አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሸቀጦችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ፓስታና ማካሮኒ ES 1055:2005
- የልብስ ሳሙና CES 42-2013
- የገላ ሳሙና CES 44-2013
- ስፖንጅ ፍራሽ
- የቆርቆሮ ሚስማር CES: 2013(ES:95-200)
- ብርድ ልብስ
ስለዚህ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባዋል፡፡
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ምርት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ሰኔ 18 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስልክ ቁጥር 0113690791/0113692647/01113692439 www.eide.com.et
በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት