የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡– ECWCT/NCB/PW/03/2013
- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የGranite paint የአቅራቦትና ገጠማ ሥራ ለአራት ፐብሊክ ሰርቪስ ፕሮጀክቶች ግዥ ለመፈፀም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመገዘቡ ብቁ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላው ኮንትራት ዋጋ 0.5% (ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ) ነገር ግን ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ) የማይበልጥ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፣ ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር ተዛማጅ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6፡30 ሰዓት በግዥ መምሪያ (የሕንፃ ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ግዥ ቡድን) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖታ እስከ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፤00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨጓታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱትመስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታ ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬስን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው የግዥ መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ከመገናኛ ወደ አያት በሚወስደው መንገደ በግራ በኩልጉርድሾ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ
200ሜትር ገባ ብሎ አንድነት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡-+251-118723086
ፋክስ፡+25111667 6090
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 21952/1000 አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን