ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት
የማሰሪያ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢህሳን ወላጅ አልባ መርጃ ድርጅት በ1993 ዓ.ም የተቋቋመና በዳግም ምዝገባ የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ማህበር ነው፡፡ ከጥር (January 1 2019) እስከ ታህሣስ (December 31) 2019 ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ከታች የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ በማስገባት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
መሟላት ያለባቸው ሰነዶችና መስፈርቶች
- የኦዲት ስራ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ለ 2012 ዓ.ም የታደሰ
- የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ ያለው
- በኦዲት ሥራው ላይ የሶስት አመት የስራ ልምድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin Number
- የኦዲት ሥራውን የሚያጠናቅቁበት እና ሪፖርት የሚያስረክቡበት ጊዜ ገደብ
- የኦዲት ሥራውን ለመስራት የሚያስከፍለውን ገንዘብ መጠን Audit Fee
ስልክ ቁጥር ፡ 0913776691/ 0911309145 / 0913595059
አድራሻ፡– አየር ጤና አደባባይ ወረድ ብሎ
ኢህሳን ወላጅ አልባ መርጃ ድርጅት