የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን
- የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፣
- የተማሪዎች መቀመጫ ወንበሮች፣
- ኮምፒውተሮችና ሌሎች እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም እቃዎቹን መግዛት ለሚፈልጉ መርካቶ ጣና ገበያ ፊት ለፊት ማርስ የገበያ ማዕከል አ/ማህበር በሚገኘው ጽ/ቤታችን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 739 በመገኘት የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የሚገዙበትን ዋጋ በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እቃዎቹን ከሰኔ 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 20/2012 ዓ.ም ድረስ በጽ/ቤቱ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በድርጅታችን ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በአዋሽ ባንከ አ.ማ ማዘዣ ከፍያ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም፡፡
- አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– በኮቪድ 19 ምክንያት ጨረታው ሲከፈት መሰብሰብ ስለማይቻል አሸናፊዎችን በጽ/ቤቱ የምንለጥፍ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ስልክ – 0912 12 35 14/ 0111 82 76 470
አፍሪካ ሪል ስቴትና የገበያ ማዕከል
አክሲዮን ማህበር