የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አፍሪካ ሕብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2013 ዓ.ም የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1 የደንብ ልብስ—የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1000
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች– የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1000
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1000
- ሎት 4 ፈርኒቸር –የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1000
- ሎት 5 ላፕቶፕ እና ፕሪንተር—- የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን1000
- ሎት 6 የስፊት የእጅ ዋጋ——- የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 500
በዚህም መሠረት፡
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በመንግሥት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ቼክ/ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በአፍሪካ ህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለጨረታ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአሥረኛው ቀን በ7፡30 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በአፍሪካ ህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታ ሰነድና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ድረስ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል።
- ሣምፕል የማያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን ት/ቤቱ እንደማያወዳድር ከወዲሁ ስናሳውቅ ተወዳዳሪዎችም ለተወዳደራችሁበት ዕቃ ሣምፕል እንድታቀርቡ ከወዲሁ ስናሳውቅ መምጣት የማይችሉ ሣምፕሎች ከሆነ ሣምፕል በሚቀመጥበት ክፍል የጥራት ኮሚቴ መጥቶ እንዲያይ አድራሻዎትን እንዲያስቀምጡ የጥራት ኮሚቴ መጥቶ የሚያየውን ሣምፕል ቀድመው በፎቶ እንዲያስገቡ እናሳውቃለን::
- ከአሽናፊው ድርጅት ግዥ ክፍል 20% ቀንሶ ወይም 20% ጨምሮ መግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መሉ በመሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– በልደታ ክ/ከተማ ልደታ ጤና ጣቢያ ገባ ብሎ ወጣት ተሀድሶ ግቢ ውስጥ
የት/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡– 0118682427 / 0118682410/0118682457/0118685774
አፍሪካ ሕብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት