የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መ/ቁጥር 2/2012 ዓ.ም
አፄ ቴዎድሮስ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2012 ዓ.ም ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት ቁ.
|
የሎት ዝርዝር
|
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
1,000 ብር |
ሎት 2 |
አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች |
1,000 ብር |
ሎት 3 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
1,000 ብር |
ሎት 4 |
ቋሚ ዕቃዎች |
2,000 ብር |
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡
- በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የሚገኙና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ ቫትን የጨመረ መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 ብር (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡–ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብሎ አክሱም ሕንፃ ጎን
ስልክ ቁጥር፡-0115576172
ማሳሰቢያ፦ የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ሙሉውን ሰነድ ሳይቆራረጥ ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በ2 ፖስታ አሽጋችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች በኮፒው የጨረታ ሰነድ ውስጥ
በማስገባት ሊቀርቡ ይገባል፡፡
የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 ይሆናል፡፡
ቂ/ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት አፄ ቴዎድሮስ አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት
አዲስ አበባ