የማተሚያ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ
አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ በሚገኘው ቢሮ የሚገኝ የማተሚያ ክፍል በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል
በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የቢሮውን ኪራይ ዝርዝር ሰነድ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ከአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ሂሣብ ክፍል የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሣ ብር/ በመክፈል ከሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ብር 10,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ወርሃዊ የኪራይ ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ኘሮፖዛል በመለየት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም 6:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ሲፒኦ ያልቀረበበት፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሌለው እና በጨረታው ሰነድ የተቀመጠውን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል
- ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም
- ጨረታው ሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በ8:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል በ15 ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ጋር ህጋዊ የውል ስምምነት ማድረግ ይኖርበታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካነኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተ.ቁ |
የክፍሉ ማተሚያ አይነት፣– |
ስፋት |
በክፍሉ የሚገኙ መገልገያዎች |
1 |
ማምረቻ |
410×510 |
|
2 |
ፊልም ማጠቢያ |
380×410 |
|
3 |
ምርት ማስቀመጫ |
190×520 |
|
4 |
ተመርቶ ያለቀ ህትመት መልቀሚያ ማስተካከያ፣ መጠረዣ ማስፊያና ማፈፊያ ክፍል |
490×530 |
|
5 |
ፊልም ማዘጋጃ |
2×210 |
|
ለተጨማሪ መረጃ
ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ
ግሎባል ሆቴል በስተጀርባ አዲስ አበባ
ስልክ ቁጥር 0114-666417/0114-651212