የጨረታ ማስታወቂያ
የሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ
- ሎት 1 ፡ የሠራተኛ የደንብ ልብስና ጫማዎች ግዥ
- ሎት 2 የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ የግዥ መለያ ቁጥር፡– አአዩ /ብግጨ/ደ/01/2013
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሠራተኞች የደንብ ልብስና ጫማዎች ግዥ ተጫራቾችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተጠቀሰውን የሠራተኞች የደንብ ልብስና ጫማዎች ግዥ
- ሎት 1፡– የሠራተኛ የደንብ ልብስና ጫማዎች ግዥ
- ሎት 2 የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ላይ ለማሰተፍ ብቃት ያላችሁ ተጫራቾችን በታሸገ ኤንቨሎፕ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
3. ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት የመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ሥነ–ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል፡፡ ሎት 1፡– የሠራተኛ የደንብ ልብስና ጫማዎች ግዥ ሎት 2 የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታው የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጋባዥ ተጫራች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የ2012 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዌብሳይት ላይ ፕሪንት አርጋችሁ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡
4) ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በቁጥር 7 (ሀ) በተላፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡ በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የህጋዊነት ማስረጃ ይዞ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ያለክፍያ በነፃ ማውስድ ይችላሉ፡፡
5) የማጫራቻ ሠነድ ለማስገባት ከዚህ በታች በቁጥር 7 «ለ» በተገለፀው አድራሻ እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቁጥር 7«ሐ» በተጠቀሰው አድራሻ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታውን ሰነድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል፡፡
6) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ለሎት 2 ብር 50,000.00 (ብር ሃምሳ ሺህ ብር) ለየብቻ በሁኔታ ላይ ያልመሰረተ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ “CPO” ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሰራት ማስያዝ ወይም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. የጨረታ ሰነድ የሚወስዱት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ በአዲሱ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 314 ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ሀ/ ጨረታው የሚገባው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200፣ለ/ ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
8) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ዋናው ግቢ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 314
ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው ስም አበበ ደመመው
ስልክ ቁጥር 251 111 22 00 0/ 09 11 44 04 57
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ