የጨረታ ማስታወቂያ 02/2013
አደአ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዢ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የደን ዘር፣
- ሎት 2. የተቀቀለ እንጨት እና ያጥር ሽቦ በጥቅል፣
- ሎት 3. የምግብ እህሎች እና ተያያዥነት ያላቸው በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፣ የቲን ተመዝጋቢ እና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 50.00(ሃምሳ) በኢትዮ.ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000011143656 በመክፈል በአደአ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በማግስቱ፡ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጽ/ቤታችንየሚያጫርትባቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ወይም ከውስጥ በመተው ማዘዝ ይቻላል።
- የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ በመምጣት ገቢ ያደርጋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ( CPO) ማስያስዝ አለባቸው::
- በጨረታው የተሸነፉትን ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሞሉት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሠነዶቻቸው ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክከል ጽፈው ማህተም በየገጽ በማድረግ መፈረም አለባቸው፡፡
- አሸናፊዎች በሚገቡት ውል ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለውል ማስከበሪያ በዋስትና ሰነድ የተያዘ (CPO) ውል መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ተይዞ ይቆያል።
- ከዚህ በላይ በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና ተያይዞ (CPO) ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒው ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መግባት አለበት።
- በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለመ/ቤቱ ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 ወይም ቁጥር 8 ቅሬታውን ማቅረብ የችላል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር፡– 011 4 335405/011 433 8590
በምሥራቅ ሸዋ ዞን የአድአ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት