ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ገ/ኢ/ትብ/ቢሮ የአዊ ብሔ/አስ/ገ/ኢ/ትብ/ዋና መምሪያ አንከሻ ጓጉሣ ወረዳ ገን/ኢኮ/ ትብ/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ልዩ ልዩ የቋሚ አላቂ እቃዎች እና የጽዳት እቃዎች
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 3 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቃ ጨርቅ
- ሎት 4 የተዘጋጀ የደንብ ልብስ
- ሎት 5 የስፖርት መምህራን ትጥቅ እና የስፖርት ቁሣቁስ
- ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ካሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የሚገዛው የግዥ መጠን ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ቲን ሰርተፊኬትና ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አን/ጓ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት የክፍያ ሂ/ማ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 በማይመለስ ብር 50 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የማወዳደሪያ ስርዓቱ በሎት አሸናፊ የሚመረጥ ይሆናል፡፡
- የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመምሪያ የገቢ ደረሰኝ/መሂ-1/ ገቢ በማድረግ የደረሰኙ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዣ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አንከሻ ጓጉሣ ወረዳ ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ16 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሣጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አንከሻ ወረዳ ገን/ኢ/ትብ/ጽ/ ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 08 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን /የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸወ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ አንከሻ ጉጉሣ ወረዳ ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ድረስ በራሣቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ እና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582240520/0582240003 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአንከሻ ጓጉሣ ወ/ገን/ኢኮ/ትብ/ጽ/ቤት