አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
3 ደብል ጋቢና ፒካፕ እና 1 ባስ 12
መቀመጫ ሚኒ ባስ ስአንድ ዓመት
ለመከራየት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ከአንድ/019/2013
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 3 ደብል ጋቢና ፒካፕና 1 ባለ 12 መቀመጫ ሚኒ ባስ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በዚሁ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩና ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት፤ በመንግስት ዕቃና አገልግሎት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የተሰጠ ፈቃድ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ዋናው መስሪያ ቤት መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከሚዘጋበት ሰዓት ቀደም ብሎ ቢሮ ቁጥር 16 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሶፍት ኮፒ ስሲዲ የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁሉም የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ዋናው መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቶት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበተ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011629 31 61፣011 629 4184
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ
አገልግሎት ድርጅት