አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
የስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች መገልገያ ግብአቶች
ግዥ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አከአአድ
002/2013
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
- የስቴሽነሪ እና
- የጽዳት እቃዎች መገልገያ ግብዓቶችን በምድብ በመከፋፈል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር በዚህ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ሆኖ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ በብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች ዝርዝር መስፈርትና ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚያቀርቡት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 2% /ሁለት በመቶ/ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በድርጅታችን አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሥም በማስያዝ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከሚዘጋበት ሰዓት ቀደም ብሎ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የሎት ዓይነት ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ እና የዕቃዎች ናሙና ላይ የራሱን ድርጅት ስም፣ ፊርማና ማህተም በግልጽ በሚታይ ቦታ መጻፍ እና ማተም አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሀምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ዋናው መስሪያ ቤት መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0965 0014 65፣ 0965 00 21 65
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
አዲስ አበባ