አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሱት
ድርጅት የሠራተኛ የሥራ አልባሳትና አደጋ መከላከያ እና
የስፖርት ትጥቆችና የስፖርት መሣሪያዎች
ግዥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አከአአድ 001/2013
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የሠራተኛ የሥራ አልባሳትና አደጋ መከላከያ እንዲሁም የስፖርት ትጥቆችን በምድብ በመከፋፈል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቶች በጨረታ ለመወዳደር በዚህ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ሆኖ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቶች የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ዋናው መስሪያ ቤት መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ በብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የሠራተኞች አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ ዝርዝር መስፈርትና ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚያቀርቡት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 2% /ሁለት በመቶ/ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በድርጅታችን አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ስም በድርጅቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በፖስታ ውስጥ በማስገባትና በማሸግ ጨረታው ከሚዘጋበት ሰዓት ቀደም ብሎ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ አይነት ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዱ ተጫራች በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ እና የዕቃዎች ናሙና ላይ የራሱን ድርጅት ስም፣ ፊርማና ማህተም በግልጽ በሚታይ ቦታ መጻፍ እና ማተም አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ነሐሴ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ዋናው መስሪያ ቤት መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስልክ ቁጥር 096500 14 65/ 0965002165
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ
አገልግሎት ድርጅት
አዲስ አበባ