ያገለገሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሲገለገልባቸው የነበሩ
- የተለያዩ ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶች ማለትም ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- የውሃ መሣቢያ ሞተሮች፣
- ጀነሬተር፣
- የሚክሰር ሞተር፣ ቫይብሬተር እንዲሁም
- አላቂ ዕቃዎች ማለትም ኤችዲፒኢ ፓይፕ፣ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች/መዶሻ፣ አካፋ፣ ቁርጥራጭ ብረት እና ሌሎች ዕቃዎች/፣ ፊቲንግ፣
- የመኪና ዕቃ መለዋወጫዎች፣
- የመኪና ጎማዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ባ/ዳር ቀበሌ 14 ከቻይና ካምፕ ፊት ለፊት ከአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ተከታታይ ቀን 8፡00 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 3200414/3494 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር