የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ቤቶቹ በሚገኙበት ቦታና ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት ) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል::
- መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌለበት ይካሄዳል::
- የጨረታው አሸናፊ በሚገዛው ቤት ላይ ከስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ይከፍላል::
- የጨረታው አሽናፊ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ግብርና ታክስ እንዲሁም የሊዝ ክፍያዎች ካሉ ይከፍላል::
- በተራ ቁጥር 2 እና 3 በተጠቀሱት ንብረቶች ላይ ገዢ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (ቫት) ይከፍላል::
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 07 11፣ 0115 54 67 36/37 አዲስ አበባ በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
- ተጫርቶ ያሸነፈና ከፊል ብድር መውሰድ ለሚፈልግ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊፈቅድ ይችላል:: ሆኖም ብድር የሚፈቅደው ባንኩ የሚጠይቀውን ማንኛውንም የብድር መስፈርት ለሚያሟላ ብቻ ነው::
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ እዳ |
የመያዣ ሰጪው ስም |
ህንፃው የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት |
ቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 |
አቶ ዘላለም ደስታ |
እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም ብር 675,953.35 |
ተበዳሪው |
ሞጆ ቀበሌ 01 |
469,750.00 |
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
መኖሪያ ቤት |
160 ካ.ሜ |
4064/2008 |
በድጋሚ |
2 |
ድል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
እስከ መጋቢት 27ቀን 2011 ዓ.ም ብር 13,857,360.20 |
ተበዳሪው |
ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 1-05 |
14,173,927.00 |
መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
ለሆቴል አገልግሎት እየሰጠ ያለ ቤት |
3,000 ካ.ሜ |
6328 |
በድጋሚ |
3 |
አቶ ክብሮም ይርጋ |
እስከ ህዳር 16 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ብር 11,812586,82 |
አቶ ታደሰ በዛብህ |
ሰበታ ከተማ |
6,584,336.00 |
ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
G+2 መኖሪያ ቤት |
400 ካ.ሜ |
ሰ/6936/99 |
በድጋሚ |
4 |
አቶ ሱራፌል ተሾመ |
እስከ ጥር 1 ቀን 2012 ድረስ ብር 1,875,828.05 |
ተበዳሪው |
አ.አ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ ወረዳ 15 |
3,220,000.00 |
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
G+2 መኖሪያ ቤት |
1,130ካ.ሜ |
ወ15/ውዝ01/94/2607/01 |
ለመጀመሪያ |
5
|
ወ/ሮ እመቤት ስዩም |
እስከ 05/05/2012 ዓ.ም. ድረስ ብር 3,218,685.01 |
አቶ ኃይሉ ሰብስቤ |
አደማ ከተማ ቀበሌ 01(ጎሮ) |
4,692,438.00 |
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡00-500 |
5፡00-5፡30 |
ለመኖሪያ B+G+2 |
262.3ካ.ሜ |
2323/2001 |
ለመጀመሪያ |
ወ/ሮ አባይነሽ ጀንበር |
አሰላ ከተማ ቀበሌ 07 |
988,428.60 |
መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡00-500 |
5፡00-5፡30 |
ለመኖሪያ |
468 ካ.ሜ |
522/289/87 |
ለመጀመሪያ |
|||
አሰላ ከተማ ቀበሌ 09 |
1,998,000.00 |
መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም |
ለመኖሪያ |
480 ካ.ሜ |
1876/30597 |
ለመጀመሪያ |