የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ
ቁጥር 001/2013
አቢሲኒያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለት/ቤቱ መምህራንና ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- የስፖርት ዕቃዎች፣
- ቋሚ የቢሮ እና አላቂ ዕቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ እና
- ህትመት ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በሙሉ ወይንም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ አንድ መቶ ብር /100.00 ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ሙሉ የጨረታ ሰነድና ዋጋ የያዘ ዝርዝር ሰነድ ኮፒውንና ዋናውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ናሙና በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 1% የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
ተ.ቁ. |
ሎት |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን |
በ% |
1 |
ሎት 1 |
ለጽዳት ዕቃዎች |
01/2013 |
1700 |
1% |
2 |
ሎት 2 |
ለስፖርት ዕቃዎች |
01/2013 |
680 |
1% |
3 |
ሎት 3 |
ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
01/2013 |
1600 |
1% |
4 |
ሎት 4 |
ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች |
01/2013 |
800 |
1% |
5 |
ሎት 5 |
የደንብ ልብስ ጨርቅ |
01/2013 |
2500 |
1% |
6 |
ሎት 6 |
የደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ |
01/2013 |
250 |
1% |
7 |
ሎት 7 |
ለህትመት ሥራ |
01/2013 |
50 |
1% |
5. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ከአሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ በአስር /10/ ቀን ውስጥ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ት/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
7. በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
8. ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ መሰረዝ መብቱ፡ የጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0112 73 72 89 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የት/ቤቱ አድራሻ፡– ከጳውሎስ ሆስፒታል ወደ መድሃኒዓለም ት/ቤት በሚወስደው መንገድ ከኩላሊት ንቅላና ተከላ ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ፡፡
ስልክ ቁጥር 011 273 29 79 ፖስታ 160248
በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ወረዳ 5
የአቢሲኒያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት