በድጋሚ የወጣ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2012
አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሊያስገነባቸው የፈለገውን የግንባታ ስራ የሚሠሩ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ቁጥር |
የስራው ዓይነት |
የሚሰሩበት ወረዳ
|
ደረጃ |
የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን |
የጨረታ ማስገቢያ ቀን
|
የጨረታ መከፈቻ ቀን |
1 |
ወረዳ 03 ጤና ጣቢያ ድንገተኛና ካርድ ከፍል፣ ቲቢ ክፍል፣ የኦዲቴብል ፋርማሲ ግንባታ፣ የአጥር ግንባታ፣ የጥበቃ ቤት እና ጀነሬተርና ላውንደሪ ከፍል ግንባታዎች
|
ወረዳ 3 |
GC5/ BC5 እና ከዚያ በላይ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 10 ሠዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀን ጀምሮ 11 ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሠዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት 11ኛዉ ቀን የስራ ቀን ጠዋት 4፡30 ጀምሮ
|
2 |
ወረዳ 09 ዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ት/ቤት ሜዳ ግንባታ
|
ወረዳ 9 |
GC5/ BC5 እና ከዚያ በላይ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 10 ሠዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀን ጀምሮ 11 ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሠዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት 11ኛዉ ቀን የስራ ቀን ጠዋት 4፡30 ጀምሮ
|
- በዘርፉ 2012 የታደሰ ህጋዊ ፈቃድያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ዋናውንና ኣንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ሆነ አማካሪ ከመስተዳድሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ተመዝግቦ የብቃት ማረጋገጫ ወይም የአጭር ምዝገባ ሰርተፊኬት ሳይዝ በሴክተሩ መሳተፍ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር /በመክፈል በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 3ተኛ ፎቅ የምህንድስና ግዥ ቡድን ቀርበው ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውና (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ ።
- ጨረታው የሚከፈተው 11ኛው ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተወዳዳሪዎች ወይንም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond 70,000 ብር ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ለ90 ቀናት የሚያገለግል ሆኖ ከኦሪጅናል ቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- በተጨማሪነት ስራውን በምን ያህል ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ የሚገልጽ የስራ መርሃ ግብር /ወርክ ስኬጁል/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ ኣንድኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱንና የተወዳደሩበት ስም በመጻፍ በሰምታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተቋራጮች የስራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፕን በሰም በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን በአራዳ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት ይህም ከሆነ ተጫራቾች ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
- በኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በወጡና በሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች ላይ ተቋራጭ ከአንድ በላይ ጨረታ መሳተፍ አይቻልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ አ/ክ/ከ/ኮ/ጽ/ቤት መጠየቅ ይቻላል!የአራዳ ክፍስ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት