የጨረታ መዝጊያ ቀን ለማራዘም የወጣ ማስታወቂያ
አምቦ ዩነቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት
- በሎት 1 የህትመት ሥራ አገልግሎት
- በሎት 2 የትርጉም ሥራ አገልግሎት
- በሎት 3 የተለያዩ የተማሪዎች መገልገያ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ፈርኒቸሮች እና
- በሎት 4 የእንስሳት መኖ ግዥ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ኅዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም በታተመ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ በመሆኑም በእያንዳንዱ ሎት የተገለፁት አገልግሎቶች እና ግዥዎች የጨረታ መዝጊያ ቀን ከኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ታኅሣሥ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ ስለሆነ የጨረታ ሰነዱን እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የግዥ ዳይሬክቶሬት አዲሱ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 329 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ታኅሣሥ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የስብሰባ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አምቦ ዩኒቨርሲቲ