የጨረታ ማስታወቂያ
የአማን-ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 በጀት ዘመን በሻሻቃ ቀበሌ ሊያሰራ ላቀደው የመማሪያ ክፍል ግንባታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቹን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- የደረጃ ቢሲ(BC/GC6 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጣበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያለማል የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፡ የት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፤የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት በማቅረብ በሚዛን አማን ከ/አስተዳደር አማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 16 የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 300 ብር በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 45,000 (አርባ አምስት ሺ ብር) በን፡ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፣
- ተጫራቾች የገቡትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በሰም በማሸግ እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም መምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናልና ኮፒ የሚል ፅሁፍ በግልፅ የሚታይ ቦታ መፃፍ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፤የተጫራቹ አድራሻ እና የተወካዩ ስልክ ቁጥር በመግልዕ መፃፍ አለበት፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚታሸገው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በአማን ፖሊ ቴክ/ኮሌጅ ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል::
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛ ቀን በአማን-ፖሊ ቴክ/ኮሌጅ ውስጥ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በደቡ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በቤንች ሽኮ
ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ