ያገለገለ ጀነሬተር ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ኃ/የተወ/የግል ማህበር ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ በዝርዝር የቀረበውን ያገለገለ ጀነሬተር ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
SN |
Item and description
|
UOM
|
Quantity
|
Remark
|
1 |
Dorman Generator 1000 KVA / 800 KW Containerized in a 40 FT (not silent), Container with Abato Control,380 – 400 Volt / 50HZ 40 Degrees Celsius ambient temperature Produced in Stafford, England Date of production: 06 / 1994 In running condition, but in need of maintenance. |
Piece
|
1 |
|
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ::
- ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት ቅፁ በሚፈቅደው መሰረት ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ጀነሬተሩ ያለበትን ሁኔታ ቢሾፍቱ በሚገኘው በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት ከጥቅምት 2 እስከ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ማየት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ የጨረታ ሰነድ በመሙላት የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተምና ፊርማ አስደግፎ በሰም በታሸገ እስከ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ማስገባት አለባቸው:: የጨረታ ሳጥን በቀኑ 3፡30 ይታሸጋል:: ከዚያም በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥን ይከፈታል:: ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በተባለው ቀንና ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን በማሸነፉ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ ጽ/ቤት መቅረብ ውል በመዋዋልና ውሉ ሲያበቃ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 1% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት::
- የጨረታው አሸናፊ ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ በድርጅቱ በሚሰጠው የቅበላ ዕቅድ መሰረት በውሉ በተጠቀሱት የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለድርጅቱ ማስረከብ አለበት::
- ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስረከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፤ አለማ ካውዳይስ መኖ ኃ/የተ/የግል ማህበር
ደብረ ዘይት(ቢሾፍቱ) ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 3190 (ዝቋላ
መንገድ ከአሜሪካን ብረታ ብረት ማቅለጫ አጠገብ)
ስልክ ቁጥር +251 11 433 06 62/+251 11 433 52 42
አለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ኃ/የተ/የግል ማህበር