ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚክሰር ትራክ ፣ ዳምፕ ትራክ (ገልባጭ መኪና) ኪራይ እና የአሸዋ አቅርቦት ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተዘጋጀ አርማታ በማምረት እና በማቅረብ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ፤ ለዚሁ ስራ ግብዓት የሚሆን አሸዋ በዘላቂነት ማቅረብ የሚችል እንዲሁም 9 ሜ.ኩ. እና ከዛ በላይ የመጫን አቅም (Design Capacity) ያላቸውን ሚክሰር ትራኮች እና ዳምፕ ትራክ (ገልባጭ መኪና) በጨረታ አወዳድሮ በመከራየት ለማሰራት ይፈልጋል::
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ አቅራቢዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች 1.1. የ 2012 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል 1.2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ 1.3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ኦሪጅናል ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ከ 15/10/2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት በዋና ቢሮ ወሎ ሰፈር መስሪያ ቤት ከፋይናንስ መምሪያ ክፍል መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክሜንት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦክስ የሚያስገቡበት ቀን 29/10/2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ጨረታው ይከፈታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ) ወይም በባንክ ጋራንቲ 10000 (አስር ሺህ) ብር በታሸገ ፖስታ ከፋይናንሻል ዶክመንት ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ 3 ቀናት ውስጥ ውል ተዋውለው ወደ ስራ መግባት አለባቸው::
ሚክሰር ትሪኮች አና ዳምፕ ትሪክ (ገልባጭ መኪና) |
የአሸዋ አቅርቦት |
6. ተጫራቾች የታደሰ የመኪናባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ በሊቢሬ/ያላቸው በተጨማሪም የማሽነሪ ኪራይ አከራይ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
7. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ የሹፌር አበል እና ደሞዝ ያካተተ መሆን አለበት:: ነገር ግን ነዳጅ በተከራይ የሚሸፈን ይሆናል:: 8. ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ዋጋ በትክክለኛ የመጫን አቅማቸው (Actual Capacity) መሆን አለበት
|
6. ተጫራቾች በግብአት አቅርቦት ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው:: 7. ተጫራቾች የሚያስገቡት የመጓጓዣ ዋጋ ያካተተ መሆን አለበት:: 8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት አሸዋ ሃገራዊ የጥራት መስፈርት Standard) የጠበቀ መሆን አለበት::
|
9. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርቶ ዋጋ ማስገባት አይችሉም::
10.በጨረታ ያሸነፈው አካል ለሌላ ሦስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችልም::
11.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- ከተራ ቁጥር1 እስከ 5 እና ከ 10 እስከ 12 ያሉት ለሁሉም ተጫራቾች የሚጠበቅባቸው መስፈርቶች ናችው::
አድራሻ: ጎተራ ! ወንጌላዊት ህንፃ ሳይደርሱ ፤ ካስ ታወር ጎን
የመጽሀፍ ቅዱስ ኮሌጅ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308 ወይም 303
ስልክ ቁጥር 0118225392/0911616124/0984715370