የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጸውን የከባድ መኪና ጎማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ተ.ቁ |
የከባድ መኪና 12.00 R20 |
መለኪያ |
የጎማ አይነት (ብራንድ) |
ያንዱ ዋጋ ከቫት በፊት |
1 |
የፊት ጎማ 140 ከነከለመንዳሪውና ፍላፕ |
በቁጥር |
|
|
2 |
የኋላ ጎማ 560 ከነከለመንዳሪውና ፍላፕ |
በቁጥር |
|
|
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ::::
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን ጎማ የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኢትዮ ቻይና ፍሬንድ ሺፕ መንገድ kt ህንጻ 1ኛ ፎቅ ወሎ ሰፈር አ.አ. ስልክ: 251 11 4 42 19 28/0986894464 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0946-4393-94/0935-98-50-83 ግዢ ክፍል ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ባሉት 20 የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም እስከ ነሐሴ 14/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጨረታው ተዘግቶ ነሐሴ 18/2012 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ ኤማ ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ለገዢው እቃዎቹን ማስረከብ ይጠበቅበታል::
ማሳሰቢያ:-
- ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል::
- መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው