የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ለድርጅቱ ሠራተኞች 503 የደህንነት ጫማዎችን (safety shoes) በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች በመስፈርቱ (Specification) መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ::
- የሚያቀርቡትን የዋጋ ዝርዝር በግልጽ በማስቀመጥ በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት እንዲሁም የደህንነት ጫማ ናሙናውን (sample) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የጫማውን ሰነድ ወይም መስፈርት ኢትዮ ቻይና ፍሬንድ ሺፕ መንገድ kt ህንጻ 1ኛ ፎቅ ወሎ ሰፈር አ.አ. ስልክ፡ 251-1144219 28/0986894464 ግዢ ክፍል እና ድሬ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0946-43-93-94/093598-50-83 ግዢ ክፍል መተው ያለምንም ክፍያ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው::
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ባሉት 20 የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም ህዳር 5/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው ተዘግቶ ህዳር 8/2013 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- ማሳሰቢያ፡” ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል::
- መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
ድርጅቱ !