የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ከዚህ በታች የተገለጸውን እቃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች
በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን ጎማ የአንዱን ኪሎ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 7 የስራ ቀናት ኢትዮ ቻይና ፍሬንድ ሺፕ መንገድ kt ህንጻ 1ኛ ፎቅ ወሎ ሰፈር አ.አ. ስልክ፡ 251 11 4 42 19 28/0986894464 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0946-43-93-94 ግዢ ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው መጋቢት 7/2012 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለገዢው እቃዎቹን ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
ማሳሰቢያ፡–
ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ድርጅቱ !